አዲስ አበባ ታዳጊዎች የቅርጫት ኳስ ልዑክ የበላይነታቸውን አረጋገጡ
አዲስ አበባ ታዳጊዎች የቅርጫት ኳስ ልዑክ የበላይነታቸውን አረጋገጡ
የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው 9ኛው ዙር የታዳጊዎች ምዘና ውድድር፣ የአዲስ አበባ ስፖርት ልዑክ በቅርጫት ኳስ ዘርፍ ደማቅ ድል በማስመዝገብ አጠቃላይ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።
ስፖርት ልዑኩ 2 ወርቅ፣1 ብር እና 1 ነሐስ በመሰብሰብ የደረጃ ሰንጠረዡን በአንደኝነት በማጠናቀቅ አዲስ አበባ የሁሉም ስፖርቶች ማዕከል መሆኗን አረጋግጧል።
በበርካታ የስርቱ አፍቃሪያን ከፍተኛ ግምት ያገኘው አዲስ አበባ በቅርጫት ኳስ ስፖርት ልዑክ በወንዶች 5ለ5 እና በሴቶች 3ለ3 የወርቅ ሜዳልያ ሲያገኝ በወንዶች 3ለ3 ብር ሜዳልያ በሴቶ 5ለ5 የነሐስ ሜዳልያ ባለቤት ሆኗል፡፡
አዲስ አበባን ተከትለው ሲዳማ፣ ጋምቤላ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በቅደም ተከተል 2ናእስ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ አዲስ አበባ ወክለው የተሳፉ ታዳጊዎች የሜዳሊያ ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በሜዳ ላይ የሳዩት ድንቅ ብቃት ለወደፊቱ የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ተስፋ መሆናቸውን ተመልከቷል፡፡
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.