የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም የሳር ንጣፍ ስራ በይፋ ተጀመረ
የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም የሳር ንጣፍ ስራ በይፋ ተጀመረ
የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሶሴሽን በምጻረ ቃል (FIFA) ስታንዳርድ መሰረት እየተገነባ የሚገኘው የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም የሳር ንጣፍ ስራ በይፋ ተጀመረ፡፡
በዓለም-ዓቀፉ እግርኳስ ፌዴሬሽን (FIFA) በአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) እንዲሁም በ World Athletics ስታንዳርዶች መሰረት በመዲናችን አዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘው የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም የመጫወቻ ሜዳ ቅልቅል (Hybrid turf) ሳር ንጣፍ ስራ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
በአውሮፓ እና በአፍሪካ በሚገኙ ትልልቅ ስታዲየሞች ላይ ሰው ሰራሽ (Artificial turf ) እንዲሁም ቅልቅል (Hybrid turf ) ሳሮችን በማምረት እና በማንጠፍ የካበተ ልምድ ካለው የጣሊያኑ ሊሞንታ (Limonta Sport) ጋር የነበረው ንግግር በውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ኩባንያው በዛሬው ዕለት በስቴዲየሙ ተገኝቶ ዳታ የመልቀም ተግባር ጀምሯል፡፡
ስራውን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንደገለፁት በስቴዲየሙ የሚነጠፈው የሳር አይነት ቅልቅል (Hybrid) ሆኖ አይነቱም carpet type እንደሚሰኝ አሳውቀዋል፡፡
ከ90 – 95 % የተፈጥሮ ሳር እንዲሁም ቀሪው ከ5–10 % ደግሞ አርቴፊሺያል እንደሚሆን ያብራሩት ኢንጂነርዋ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ እግርኳስ ድርሳን ላይ አዲስ ገፅ የሚገልጥና ለስፖርት ቱሪዝም እንዲሁም ለውጪ ግንኙነታችንም ጭምር በጎ ፋይዳ እንደሚኖረው አያይዘው ጠቁመዋል፡፡
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.