የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሜዳ ቴኒስ ውድ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሜዳ ቴኒስ ውድድሩን በበላይነት አጠናቀቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሜዳ ቴኒስ ውድድሩን በበላይነት አጠናቀቀ።

የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 9ኛው ዙር የአገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር፣ የአዲስ አበባ ስፖርት ልዑክ በትክክለኛው የዕድሜ ክልል በመሳተፍ በሜዳ ቴኒስ ዘርፍ ደማቅ ድል አስመዝገበ

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የሜዳ ቴኒስ ውድድር፣ የአዲስ አበባ ልዑክ ለዘርፉ ከተዘጋጁት 5 የወርቅ ሜዳልያዎች መካከል አምስቱንም በብቃት በማሸነፍ የውድድሩ ሻምፒዮና ሆኗል

የታዳጊዎች ስፖርት ልዑኩ በነጠላ በሁለቱም፣ በድብልቅ፣በጥንድ የተዘጋጁ ሜዳልያዎችን ከመውሰዱ ባሻገር አራት የነሐስ ሜዳልያ ባለቤት ሆኗል

በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ሁሉም ስፖርተኞች በሙሉ የተቀመጠውን የታዳጊነት የዕድሜ መስፈርት በትክክል የሚያሟሉ መሆናቸው ያወሱት የስፓርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ ታዳጊዎቹ በሜዳ ላይ ያሳዩት ቴክኒካዊ ብቃትና ስነ-ምግባር ለሀገሪቱ የሜዳ ቴኒስ ስፖርት ትልቅ ተስፋ መሆኑን ገልጸዋል

የልዑካኑ መሪዎችና አሰልጣኞች እንደገለጹት ይህ ድል የተገኘው ታዳጊዎቹ ካሳዩት ከፍተኛ ፍላጎትና በቅድመ ውድድር ወቅት ከተደረገው ጠንካራ ዝግጅት የመነጨ መሆኑን ነው።

ሙሉ በሙሉ ታዳጊ የሆኑ ስፖርተኞችን በማሰለፍ እንዲህ ያለ ውጤት መመዝገቡ፣ ለወደፊቱ ብቁና ተጫዋቾችን ለማፍራት ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር አሰልጣኞቹ አክለዋል

ውጤቱ የልዑኩን አጠቃላይ የሜዳልያ ሰንጠረዥ ከፍ ከማድረጉም በላይ፣ በከተማዋ እየተሰራ ያለው የተተኪ ስፖርተኞች ልማት ውጤታማ መሆኑን እንደሚያመላክት ተገልጽዋል

በውድድሩ ኦሮሚያ 5 ብር 1 ነሐስ 2 ኛ ደረጃን ይዞ ሲየጠናቅቅ አማራ እና ሲዳማ ክልል አንድ አንድ ነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት አኩል 3 ኛ በመሆን አጠናቀዋል

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.