ስብዕና_ልማት_ለትውልድ፦ የጀመርነው የለውጥ ጉዞ ውጤት ማምጣት ጀምሯል! / ወጣትና ስፖርት ቢሮ/
ስብዕና_ልማት_ለትውልድ፦ የጀመርነው የለውጥ ጉዞ ውጤት ማምጣት ጀምሯል! / ወጣትና ስፖርት ቢሮ/
የካቲት 07 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ “ስብዕና ልማት ለትውልድ” በሚል መሪ ቃል ከሦስት ወራት በፊት የጀመረው የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን የማደስና የመጠገን ስራ ስኬታማ በሆነ መንገድ ቀጥሏል።
እስካሁን ባለው ሂደት ቢሮው በቁርጠኝነት ባከናወነው ስራ 42 ማዕከላትን ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲታደሱ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚገኘውን ቁጥር 2 ስብዕና መገንቢያ ማዕከል በድምቀት አስመርቀናል።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ ባስተላለፉት መልዕክት፦ ይህ ማዕከል ለምርቃት እንዲበቃ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ ክብረአለም በመለክታቸው የጀመርነው የኢኒሼቲቭ ስራ ውጤት ማምጣት መጀመሩ ለወደፊት ስራዎቻችን ትልቅ ብርታት ነው ብለዋል።
በቀጣይ ጥቂት ጊዜያት ውስጥም ሌሎች በርካታ ማዕከላትን አድሰን በማጠናቀቅ ለምርቃት የምናበቃ ይሆናል" ሲሉ የም/ቢሮ ሀላፊው አሳውቀዋል።
ቢሮው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ስብዕና ለመገንባትና ምቹ የመገናኛ ስፍራዎችን ለመፍጠር የጀመረውን ይህን ስራ በልዩ ትኩረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ክብረአለም አፅዕኖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
81Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 79 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.