#እንኳን_ደስ_አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን!!...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

#እንኳን_ደስ_አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን!! አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምዘና ውድድሩ ትክክለኛ የእድሜ እርከን ይዞ በመቅረብ፣ በርካታ ታዳጊዎችን ለአካዳማ በማስመረጥ እና በስፖርታዊ ጨዋነት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

#እንኳን_ደስ_አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን!!

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምዘና ውድድሩ ትክክለኛ የእድሜ እርከን ይዞ በመቅረብ፣ በርካታ ታዳጊዎችን ለአካዳማ በማስመረጥ እና በስፖርታዊ ጨዋነት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የካቲት 08 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በአዳማ ከተማ ከየካቲት 01 ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 9ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና የምዘና ውድድር ዛሬ ተጠናቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምዘና ውድድሩ ትክክለኛ የእድሜ እርከን ይዞ በመቅረብ፣ በርካታ ታዳጊዎችን ለኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በማስመረጥ፣ እና በላቀ ስፖርታዊ ጨዋነት የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል።

ከተማ አስተዳደሩ በ14 የስፖርት አይነቶች ከ630 በላይ የሚሆኑ የስፖርት ልዑካንን በመያዝ በውድድሩ ላይ የተሳተፈ ሲሆን፣ በተለይም በትክክለኛ የዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ታዳጊዎችን በማሳተፍ ረገድ ውጤታማ ስራ ማከናወኑ ተመልክቷል።

በዚህም ምክንያት በርካታ የከተማዋ ታዳጊዎች የብቃታቸው ደረጃ ተመዝኖ ለኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እንዲመረጡ ለማድረግ ተችሏል።

በተጨማሪም የልዑካን ቡድኑ በውድድሩ ሂደት ባሳየው እጅግ የሚደነቅ ሁለንተናዊ ስፖርታዊ ጨዋነት የልዩ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል። ሽልማቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ተቀብለዋል።

አቶ በላይ ደጀን ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት “ይህ ውጤት በከተማችን በታዳጊዎች ስፖርት ላይ እየተሰራ ያለው ስራ ፍሬ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

ትክክለኛ እድሜ ያላቸውን ታዳጊዎች በማሳተፍ ለሀገር አቀፍ አካዳሚ ማስመረጥ መቻላችን ለኢትዮጵያ ስፖርት ተተኪዎችን ለማፍራት የምናደርገው ጥረት ውጤታማ መሆኑን ማሳያ ነው” ብለዋል።

አክለውም በውድድሩ የታየው ስፖርታዊ ጨዋነት የከተማዋን ስም የሚያስጠራ መሆኑን አቶ በላይ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በጅምላስቲክ እና በሜዳ ቴኒስ፤ በቅርጫት ኳስ፣ በእጅ ኳስ እና በሴቶች ቦክስ እና በመስማት የተሳናቸው ውድድሮች አጠቃላይ አሸናፊ መሆን ችሎል።

ይህ የምዘና ውድድር ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ ታዳጊዎችን ከታችኛው እርከን አንስቶ በሳይንሳዊ መንገድ ለማብቃት ያለመ መሆኑ ይታወቃል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.