ዓድዋ አደራ፡ የአንድነት እና የሉዓላዊነት ተምሳ...

image description
- ውስጥ supporter    0

ዓድዋ አደራ፡ የአንድነት እና የሉዓላዊነት ተምሳሌት!

ዓድዋ አደራ፡ የአንድነት እና የሉዓላዊነት ተምሳሌት!

የካቲት 09 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ “ዓድዋ አደራ፤ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ደማቅ የፓናል ውይይት ከሰራተኞች ጋር አካሄደ።

በውይይቱ ላይ የድሉን ታላቅነትና ለወቅቱ ትውልድ የሚሰጠውን ትምህርት የሚዳስስ ጥናታዊ ሰነድ ቀርቧል።

የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ያለውን ፋይዳ በዝርዝር የዳሰሰ ሲሆን፤ ድሉ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ኩራትና የነፃነት ተጋድሎ መነሻ መሆኑን በሰነዱ ተበራርቷ ቀርቦል።

በተለይም የወቅቱ ወጣት የዓድዋን ድል ከታሪክነት ባለፈ ለሀገር ግንባታ፣ ለፈጠራና ለስራ ባህል መጎልበት እንደ ትልቅ "ማንሰራራት" ሊጠቀምበት እንደሚገባ በሰነዱ ተመላክቷል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የቢሮው የፀ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራን ዓድዋ የትናንት ታሪክ ብቻ ሳይሆን የዛሬው አንድነታችን መሠረት ነው ብለዋል።

አባቶቻችን በጦር ግንባር የፈጸሙትን ጀግንነት፣ እኛ ዛሬ በልማትና በሰላም ግንባር ልንደግመው ይገባል ሲሉ ገልፀዋል ።

ወጣቱ እና ሰራተኛው ከዓድዋ የሚማረው ትልቁ ቁምነገር 'የማይቻል የለም' የሚለውን ስነ-ልቦና መሆኑን አቶ ሚሊዮን አፅእኖት ሰጥተው ተናግረዋል!"

አቶ ክብረአለም ደምሴ የቢሮው ም/ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው ሉዓላዊነት የሚከበረው ዳር ድንበርን በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚም ራሳችንን ስንችል ሲሉ ተናግረዋል።

130ኛው የዓድዋ ድል ስናከብር፣ ወጣቶች የሀገርን አደራ ተረክበው በቴክኖሎጂና በእውቀት እንዲጠበቁ ለማድረግ ቢሮው በቁርጠኝነት እየሰራን መሆኑን ገልፀዋል።

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.