የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ምዘና ማካሄድ ጀመረ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም ምዘና ማካሄድ ጀመረ።
የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ምዘና ማካሄድ ጀምሯል።
ቢሮው በከተማዋ ስር የሚገኙ የክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤቶችን፣ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከላትን እንዲሁም በቢሮው የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችን አፈፃፀም የሚዳስስ ነው።
ምዘናው በዋናነት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ የተከናወኑ ተግባራትን መገምገም፤ የከተማዋን ሁለንተናዊ የስፖርት ዕድገት ለማረጋገጥ የተቀመጡ ግቦች ምን ያህል መሳካታቸውን ማረጋገጥ ሲሆን በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት ለቀጣይ ስድስት ወራት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር የሚያስችል ምዘና ነው።
የምዘና ሂደቱን አስመልክቶ የቢሮው የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ክራን በየክፍለ ከተሞቹ በመዘዋወር ምልከታ አድርገዋል።
የፅ/ቤት ኃላፊው በምልከታቸው ወቅት እንደገለጹት፣ ምዘናው ተቋማዊ ተጠያቂነትን ለማስፈንና በዕቅድ የተያዙ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብለዋል።
ይህ የምዘና መርሃ-ግብር በቀጣይ ቀናትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ከምዘናው በኋላ በሚገኘው ውጤት ላይ ተመስርቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.