2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን ስፖር...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ውድድር በድምቀት ተጠናቀቀ

2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ውድድር በድምቀት ተጠናቀቀ

የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም በተካሄደ ደማቅ የማጠቃለያ ስነ-ስርዓት ፍጻሜውን አግኝቷል።

ከጥር 23 ቀን ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው በዚህ ስፖርታዊ መድረክ ላይ የተማሪዎችና የመምህራን አሸናፊዎች የታወቁ ሲሆን፣ በዕለቱም የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ፤ ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት ባሻገር፣ የተተኪ ስፖርተኞች መፍለቂያ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

"ዓላማችን በአእምሮው ንቁ፣ በአካል ብቁ እና በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ መፍጠር ነው" ያሉት ኃላፊው፣ ስፖርት ለዚህ ግብ ስኬት ቁልፍ ሚና እንዳለው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው፣ በከተማዋ ሰፊ የስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው በከተማዋ በአጠቃላይ 2,851 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ተናግረዋል።

የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በብዛት መገንባታቸው ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት እንዲሁም

ወጣቱ ትርፍ ጊዜውን በስፖርት በማሳለፍ ራሱን እንዲጠብቅና ጤናማ አምራች ዜጋ እንዲሆን ያስችላሉ ብለዋል።

የትምህርት ቤቶች ስፖርት ውድድር በቀጣይ 10 አመታት አሸናፊ ብሔራዊ ለመገንባት እንደሀገር የተያዘውን ግብ ለማሳካት ትልቅ ሚና እንዳለው አቶ ዳዊት ተናግረዋል።

+5

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

62Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 60 ሌሎች

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.