2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን ስፖር...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ውድድር አሸናፊ ትምህርት ቤቶች የዋንጫ ሽልማት ተበረከተ

2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ውድድር አሸናፊ ትምህርት ቤቶች የዋንጫ ሽልማት ተበረከተ

የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት 2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር ሻምፒዮና ለሆኑ ክፍለ ከተሞች የዋንጫ ሽልማት ተበረከተ

በመምህራን መካከል የተካሄደውን ጉለሌ ክፍለ ከተማ 4 ወርቅ፣ 4 ብር፣ 1 ነሐስ አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላመሚ ሆኗል፡፡

በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል በተካሄደው ጠንካራ ፉክክር 13 ወርቅ፣ 9 ብር፣ 7 ነሐስ በመሰብሰብ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሻምፒዮና ሆኗል

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 8 ወርቅ፣ 3 ብር፣ 2 ነሐስ ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል

በባህል ስፖርቶች በተካሄደው ውድድር 10 ወርቅ፣ 2 ብር በማስመዝገብ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የድርብ ድል ባለቤት ሆኗል፡፡

በስፖርት ውድድር ዘንድ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን ስፖርታዊ ጨዋነት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሲወስድ ደማቅ ትርኢት በማሳየት የሽብርቅ ዋንጫ ሽልማቱን ከዕለቱ የክብር እንግዳ እጅ, ተቀብሏል፡

የሽብርቅ ዋንጫ በተካሄደው ፉክክር ገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት 2ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ አቃቂ ክፍለ ከተማ እና አራዳ ክፍለ ከተማ 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡

የ2ኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ እና የመምህራን ውድድር በተሳፎ አንደኛ በመሆን ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

https://linktr.ee/YouthandSport1

+23

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

20አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 19 ሌሎች

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.