ቢሮው ስብዕና ልማት ለትውልድ የወጣቶች ፌስቲቫል እና የማዕከላት የማስዋብ ኢንሼቲቭ ስራ ላይ ውይይት አካሄደ
ቢሮው ስብዕና ልማት ለትውልድ የወጣቶች ፌስቲቫል እና የማዕከላት የማስዋብ ኢንሼቲቭ ስራ ላይ ውይይት አካሄደ
የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስብዕና ልማት ለትውልድ በሚል መሪ ቃል ለሚካሄደው 9ኛው የወጣቶች ፌስቲቫል እና ማዕከላት የማስዋብና ለወጣቶች ምቹ የማድረግ የቢሮዉ ኢንሸቲቭ ስራ ላይ ከዘርፉ ባለሙያዎቸ ጋር ውይይት አካሄደ
በዘንድሮ ውድድር 113 ወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፍሬዎች ከኪነጥበብ ባሻገር በፈጠራና ስራ እንደሚሳተፉ ያወሱት ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ክብርዓለም ደምሴ በማዕከላት ለወጣቶች ሁለንተናዊ ለውጥ ማዕከላት የሚሰጡት አገልግሎቶች የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል
አርባ ሁለት የወጣት ስብዕና ማዕከላት በኢኒሼቲቩ ማራኪ መደረጋቸውን ይፋ ያደረጉት አቶ ክብር- ዓለም ቢሮ ከሚሰራቸው የፓይለት ስራዎች በተጨማሪ ለወጣቶች ከሱስ ማገገሚያ ማዕከል ለመስራት ፍላጎት ላላቸው ማእከላት አስፈላጊው እገዛ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል
የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ወጣቶች በአካል፤በአዕምሮና በስነ-ልቦና የሚበቁባቸው ተቋማት ናቸው ያሉት አቶ ክብርዓለም ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የሚየሳዩ ፌስቲቫሎች እንደሚስፋፉ አሳውቀዋል፡፡
ስብዕና ልማት ለትውልድ የወጣቶች ፌስቲቫል እና የማዕከላት የማስዋብ ኢንሼቲቭ ስራ ላይ ገለጻ ያደረጉት የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ሳሙኤል ምትኩ ፌስቲቫሉ ወጣቶች ያላቸውን እውቀትና ክህሎት እንዲሁም የፈጠራ ስራዎችን ለማበረታታት ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ሳቢ፤ማራኪና ስታዳንዳቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማደረግ የተሰሩ ስራዎች በሁሉም ለማስፋፋት በትኩረት እንዲሰራ ያሳሰቡት አቶ ሳሙኤል ማእከላት አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃቸውን ለማሻሻል እንዲሁም ያለባቸውን ችግሮች በንቅናቄ ተግባር መፍታት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.