የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ይበልጥ ለማስፋፋት የሚስችለው የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ይበልጥ ለማስፋፋት የሚስችለው የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ
የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ ከፊት ኮርነር (Fit Corner) እና ከጎፈሬ (Gofere) ትጥቅ አምራች ጋር በመተባበር በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማስፋፋት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የሦስትዮሽ ስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ
ጎፈሬፊት ቱር የተሰኘው ለሁለት ዓመታት የሚቆየው ስምምነት ዋና ትኩረቱ በየአከባቢው የሚገኙ አካል ብቃት አሰልጣኞች እና ጤና ቡድኖች እውቅና በመስጥ የሚያበረታታ መሆኑን ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተመልክቷል
ስምምነቱ አዲስ አበባን የሚመጥን ዘመናዊና የተደራጀ የስፖርት እንቅስቃሴ ለማስፋፋት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው የገለጹት ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ዳዊት ትርፉ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለየት የሚያደርገው የባለሙያዎችና የትጥቅ አቅራቢዎች ተሳትፎ መኖሩ ነው ብለዋል፡፡
የስፖርት ፖሊሲውን ተግባራዊ ለማድረግ እና አካል ብቃትን በቤተሰብ ደረጃ ለማድረስ ስምምነቱ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ያወሱት አቶ ዳዊት ለወጣቱ እና ለስፖርት ቤተሰቡ ተሳትፎ ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል
ታዋቂው የትጥቅ አምራች ጎፈሬ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና ምርቶቹን ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ስምምነቱን እንደ መልካም አጋጣሚ እንደሚጠቀምበት ዋና ስራ አስኪጁ አቶ ሳሙኤል መኮንን ገልጸዋል፡፡
የፊት ኮርነር አማካሪ እና መስራች ኢንስትራክተር ነጻነት ካሳ በበኩላቸው የአካል ብቃት እንቅስቃሴው በየሳምንቱ ቅዳሜ በመደበኛነት እንዲከናወን አውስተው ስፖርትን ባህል ለማድረግ እንዲህ አይነት ስምምነቶቸ የጎላ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ስምምነቱን ተከትሎም በመዲናዋ የካቲት 21 2018 ዓ/ም የሚጀምር ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚዘልቅና በየሳምንቱ ቅዳሜ የሚከናወን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዘመቻ በይፋ እንደሚጀመር ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.