አድዋ ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ' - 130ኛው የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።
አድዋ ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ' - 130ኛው የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመዲናዋ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።
የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም - ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
130ኛውን የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ደማቅ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ሸዊት ሻንካን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
"አድዋ ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተከናወነው መርሃ ግብር፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመዲናዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የአድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን የአንድነትና የጽናት ትልቅ ትምህርት የሰጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዛሬም በልማትና በሰላም ማስከበር ስራዎች እየተደገመ መሆኑን ገልጸዋል።
ከንቲባዋ አክለውም፣ "የአድዋ ጀግኖች አባቶቻችን እና እናቶቻችን በደማቸው ያስረከቡንን ነፃነት እና ሀገር፣ የዛሬው ትውልድ ደግሞ በልማት እና በሰላም ግንባታ የራሱን 'ዳግም አድዋ' እያስከበረ ይገኛል" ብለዋል።
ይህም ትውልድ ከትናንቱ የድል ታሪክ ተምሮ፣ ልዩነቶቹን ወደ ጎን በመተው በጋራ ለአንዲት ጠንካራ እና የበለጸገች ኢትዮጵያ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ከንቲባዋ "አድዋ የጦርነት ድል ብቻ ሳይሆን የሰላም፣ የአብሮነት እና የነፃነት ተምሳሌት በመሆኑ፣ እኛም ይህንን እሴት በመላበስ ድህነትን በማሸነፍ የኢኮኖሚ አድዋችንን እውን ማድረግ ጀምረናል" ሲሉ አሳስበዋል።
በተለይም አሁን ላይ እየተመዘገቡ ያሉ ፈጣን የልማት ስራዎች እና የሰላም ማስከበር ተግባራት የዚሁ ዳግም የአድዋ የድል መንፈስ መገለጫዎች መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች በንግግራቸው አብራርተዋል።
በመድረኩ የተገኙት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ በበኩላቸው፣ የአድዋ ድል የጀግንነት ተምሳሌት መሆኑን አውስተው፣ አድዋ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ህዝቦች የድል ምልክት ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው፣ ስፖርት ከጤና ጠቀሜታው ባለፈ ህዝባዊ ትስስርን እንደሚያጠናክር ገልጸው፤ 130ኛውን የአድዋ ድል በዓል መሰል ስፖርታዊ ንቅናቄዎች መከበሩ ለሀገራዊ መግባባት ሚናው የላቀ መሆኑን አስገንዝበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.