በአድዋ ድል ፕላዛ ወጣቶችን ያነቃቃ የኪነ ጥበብ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በአድዋ ድል ፕላዛ ወጣቶችን ያነቃቃ የኪነ ጥበብ ትዕይንት ተካሄደ

በአድዋ ድል ፕላዛ ወጣቶችን ያነቃቃ የኪነ ጥበብ ትዕይንት ተካሄደ

መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከፋሲካ ኪነ ጥበብ እና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር አንድ ልብ አንድ ምት በሚል መሪ ቃል በአድዋ ድል ፕላዛ ከ10ሺ በላይ ወጣቶች የተሰታፉበት ደማቅ የኪነ ጥበብ ትዕይንት አካሄደ

ወጣቶችን ለማነቃቃት እና ለላቀ ስራ ለማበረታት ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብረ-ዓለም ደምሴ ዳንስን በተለያዩ ቅርጽ በማቀናጀት የተካሄደው ትዕይነት፣ ጤናማና ንቁ ትውልድ ለመገንባት ያስችላል ብለዋል፡፡

እንዲህ ያሉ ማራኪ መድረኮች በኮሪደር ልማት በተዋቡ ቦታዎች መካሄዱ ወጣቶች ችሎታቸውን ለበጎ ተግባር እንዲያውሉ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ያወሱት አቶ ክብርዓለም ዝግጅቱ አድዋ ድል ፕላዛ መሰነዳቱ ወጣቶች የታሪካቸውን ባለቤትነት እየተገነዘቡ ራሳቸውን በብቃት እንዲያዘጋጁ የሚያነሳሳ መሆኑ አመላክተዋል

የዝግጅት ዓላማ ወጣቱ ከመጥፎ ሱሶች ርቆ በጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ላይ እንዲያተኩር ማስቻል ነው ያሉት አቶ ክብር-ዓለም መድረኩ የእርስ በእርስ ትስስርና ማህበራዊ መስተጋብር ይበልጥ እንዲሚያጠናክር ገልጸዋል

በአድዋ ድል ፕላዛ በተዘጋጀው የአደባባይ ኪነ ጥበብ ትዕይንት ላይ በዘመናዊ ዳንስ እና በባህላዊ ውዝዋዜ የታጀበ አሰደሳች የጥበብ መድረክ ላይ ታዋቂ አርቲስቶች፣ቲክቶከሮች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ተገኝተዋል

በወጠት ስብዕና መገንቢያ ማእከል የሚሰሪ ባህላዊ እና ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ቡድኖች ከወጣቱ ጋር በመሆን በሙዚቃ ታጅበው የአገራችን ብልጽግና፣ የወጣቱን የልማት ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በዳንስ በማዋዛት ለዕይታ አቅርበዋል

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.