3ኛው የጆርካ የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

3ኛው የጆርካ የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ ውድድር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኮልፌ ክፍለ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

3ኛው የጆርካ የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ ውድድር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኮልፌ ክፍለ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

መጋቢት 06 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

ለተከታታይ አምስት ቀናት በአደይ አበባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በሁለት ዲቪዚዮን ተከፍሎ በከፍተኛ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው 3ኛው የጆርካ የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ ውድድር ዛሬ ደማቅ ፍፃሜውን አግኝቷል።

በውድድሩ ላይ በሁለቱም ዲቪዚዮኖች 20 ክለቦች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከ900 በላይ የሚሆኑ ልዑካንና ስፖርተኞችም ተሳታፊ ሆነዋል።

በአንደኛ ዲቪዚዮን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የአጠቃላይ አሸናፊ በመሆን ዋንጫውን ማንሳት ችሏል።

መቻል እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ደግሞ እንደ ቅደም ተከተላቸው 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በሁለተኛ ዲቪዚዮን በኩል የኮልፌ ክፍለ ከተማ የአጠቃላይ አሸናፊ ሲሆን፣ አራዳ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ደግሞ የ2ኛ እና የ3ኛ ደረጃ ተሸላሚ በመሆን የድሉ ተጋሪ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ውጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ሃይለጊዮርጊስ በእለቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ውድድሩ በአዲስ አበባ የሚገኙ ክለቦችና ክፍለ ከተሞች ያላቸውን አቅም የፈተሹበትና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ትልቅ መድረክ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

"እንደነዚህ አይነት ውድድሮች ስፖርተኞች በውድድር መንፈስ እንዲታነጹ ከማድረጋቸው ባለፈ፣ ከተማችን በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ መድረክ ውጤታማ የሆኑ አትሌቶችን ለማፍራት የምታደርገውን ጥረት የሚያግዙ መሆናቸውን አቶ አሰግደው ተናግረዋል።

በቀጣይም ቢሮው ለስፖርቱ እድገት የሚደረጉ መሰል የውድድር መድረኮችን በቅርበት እንደሚደግፍ የቢሮ ሀላፊው አረጋግጠዋል።

ዛሬ በተከናወነው የመዝጊያ እና የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አሰግደው ሃይለጊዮርጊስ፣ የቢሮው የስፖርት ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ፣ የወጣቶች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ እና የቢሮው የፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚሊዮን ኮራን ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ መልካሙ ተገኝ፣ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አባላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ እንግዶች ተገኝተው ለተሸላሚዎች ሽልማት አበርክተዋል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.