ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማና ለሀገር መልካም...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማና ለሀገር መልካም ገጽታ ግንባታ ልንጠቀም ይገባል” - የመዲናዋ ወጣቶች

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማና ለሀገር መልካም ገጽታ ግንባታ ልንጠቀም ይገባል” - የመዲናዋ ወጣቶች

መጋቢት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከ11ዱም ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና በወቅታዊ ዲጂታል ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው ወጣቶች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያለባቸውን ግንዛቤ በማሳደግ፣ የሚዲያ አጠቃቀማቸውን ለበጎ ተግባር እንዲያውሉ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ፤ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ ብቻ በመጠቀም የከተማቸውንና የሀገራቸውን መልካም ገጽታ የመገንባት ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በተለይም አሁን ባለው የ"ድህረ-እውነት" (Post-Truth) ዘመን፣ ወጣቶች መረጃዎችን ከመቀበላቸውና ከመጋራታቸው በፊት በትክክለኛነታቸው ላይ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባና ሚዛናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሊኖራቸው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ በበኩላቸው ወጣቱ ትውልድ በቴክኖሎጂ የታገዘ እውቀትን በመቅሰም ለራሱ ስብዕና ግንባታና ለሀገሩ ሁለንተናዊ እድገት በትጋት ሊጠቀምበት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ይህ ስልጠና ከአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በመጡና በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን፤ በዋናነት ሀሰተኛ መረጃዎችን (Fake News) መለየትና መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች፣ በዲጂታል ስነ-ምግባርና በማህበራዊ ሚዲያ የገጽታ ግንባታ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጓል።

በመጨረሻም ተሳታፊ ወጣቶች ከባለሙያዎቹ ጋር ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በስልጠናው ያገኙትን እውቀት በተግባር በመተርጎም በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረም ቃል ገብተዋል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.