ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ቁሳቁ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ቁሳቁስ ድጋፍ ለወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ተደረገ

ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ቁሳቁስ ድጋፍ ለወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ተደረገ

መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ 114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ይበልጥ ውጤታማና ለወጣቶች ምቹ ለማድረግ የሚያስችል ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ማዕከላቱን በግብዓት የማሟት ስራ ወጣቱ የእኔነት ስሜት እንዲሰማው ለማድረግ ያለመ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደደው ኃይለጊዮርጊስ ሁሉንም ማዕከላት ሳቢ እና ማራኪ የማድረግ ስራ በቁርጠኝነት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሀገር ተረካቢ ወጣቶችን በአካልና በአዕምሮ ለማነጽ ታስበው ከተገነቡ ከ60 በላይ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በራስ አቅም ማራኪ መደረጋቸው ትልቅ ስኬት ነው ያሉት ቢሮ ኃላፊው ማዕከላቱ ራሳቸውን ችለው ለወጣቶች የተሻለ ተማራጭ ስፍራ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ማዕከላቱ ወጣቶችን በስነ-ምግባር፣ በአካል ብቃትና በክህሎት ለማነጽ የሚያደርጉትን ጥረት በዘመናዊ ግብዓቶች መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን ያመላከቱት ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ክብርዓለም ደምሴ የተደገረው ቁሳቁሶች ንባብና የቴክኖሎጂ የሚያፋጥኑ ኮምፒተሮች፣ የኪነ ጥበብ ቡድን አልባሳት፣ የላይብረሪ እና የካፌ ወንበሮች መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡

የወጣቶችን የፈጠራ አቅም የሚያሳዩ እና ችሎታቸውን የሚያሳድጉበት ልዩ ልዩ ዝግጅቶች በቅርቡ እንደሚካሄዱ ይፋ ያደረጉት አቶ ክብር -ዓለም የማዕከላት ሥራ አስኪያጆች እና ባለሙያዎች የወደፊቱን ሀገር ተረካቢ ትውልድ በመቅረጽ ረገድ እየተጫወቱ ያለውን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.