ወጣት ይምረጥ፣ ሀገር ትፅና"፦ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ለምርጫው ስኬታማነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገለጹ
ወጣት ይምረጥ፣ ሀገር ትፅና"፦ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ለምርጫው ስኬታማነት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገለጹ
መጋቢት 15 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና በምርጫ ዝግጅት ዙሪያ ከክፍለ ከተማው ወጣቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ።
ይህ የምክክር መድረክ "ወጣት ይምረጥ፣ ሀገር ትፅና" በሚል መሪ ቃል የተመራ ሲሆን፣ ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የክፍለ ከተማው ወጣቶች እንደገለጹት፤ መጪው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና በሕዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ዜጋዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ወጣቶቹ አክለውም በምርጫው ሂደት ውስጥ በሰከነ መንፈስ በመሳተፍ ለሌሎች አርአያ ለመሆንና የአካባቢያቸውን ሰላም ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ወጣቱ የሀገር ባለውለታና የለውጥ ኃይል እንደመሆኑ መጠን በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል።በተለይም ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ወጣቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ በበኩላቸው፤ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ወጣቶች ለሰላም ቅድሚያ በመስጠትና በምርጫው ሂደት ውስጥ በሰከነ መንፈስ በመሳተፍ ለሌሎች አርአያ መሆን እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የክፍለ ከተማው አስተዳደርም ወጣቶች ለሚያደርጉት በጎ እንቅስቃሴ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
የውይይቱን መነሻ ሰነድ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብረአለም ደምሴ ያቀረቡ ሲሆን፤ በሰነዱም ወጣቶች በምርጫ ወቅት ሊኖራቸው ስለሚገባው ሁለንተናዊ ተሳትፎ፣ ስለ ሰላም ጥበቃና ስለ ዲሞክራሲያዊ መብቶች አጠቃቀም በዝርዝር ቀርቧል።
በመጨረሻም፣ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ወጣቶቹ ባነሷቸው የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ለሀገር ሰላምና ለምርጫው ስኬታማነት በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ በመድረስ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.