''ወጣት ይምረጥ ሀገር ትፅና''፦ የአዲስ አበባ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

''ወጣት ይምረጥ ሀገር ትፅና''፦ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ከወጣቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

''ወጣት ይምረጥ ሀገር ትፅና''፦ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ከወጣቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

መጋቢት 17 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር፣ በመጪው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ከክፍለ ከተማው ወጣቶች ጋር ሰፊ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

ውይይቱ "ወጣት ይምረጥ፤ ሀገር ትጽና!" በሚል መሪ ቃል የተመራ ሲሆን፣ ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጎልበት ያለመ ነው።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አሰግደው ሀይለጊዮርጊስ፣ ወጣቶች በምርጫ ሂደት ውስጥ ያላቸው ንቁ ተሳትፎ ለሀገር ህልውና እና ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።

ሀላፊው አክለውም፣ ወጣቶች በመጪው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በንቃት በመሳተፍ የሀገራችንን የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በፅኑ መሰረት ላይ የመጣል ታሪካዊ ሀላፊነት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ምርጫው ስኬታማ እንዲሆንና የህዝብ ድምፅ እንዲከበር የወጣቶች ሚና የማይተካ መሆኑንም አቶ አሰግደው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የዲሞክራሲ ስርዓተ ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አራርሳ በበኩላቸው፣ ወጣቶች በምርጫው ሂደት ውስጥ ቀዳሚ ተዋናይ በመሆን እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ በማድረግ የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ክብረአለም ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፣ በሰነዳቸውም ወጣቶች በምርጫው ወቅት ሊኖራቸው የሚገባ የተሳትፎ፣ የዲሞክራሲ መርሆዎችን የመረዳትና የማስፈጸም አስፈላጊነት እንዲሁም "ወጣት ይምረጥ፤ ሀገር ትጽና!" የሚለው መሪ ቃል ትርጉምና ተፈጻሚነት ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በመድረኩ የተሳተፉ የወጣቶች ተወካዮች ለሀገር ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ለመወጣትና ለምርጫው ስኬታማነት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.