የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ስፖርት ልዑካን ቡድ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ስፖርት ልዑካን ቡድን ወደ ሐረር ለሚደረገው ሀገር አቀፍ ውድድር ሽኝት ተደረገለት

የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ስፖርት ልዑካን ቡድን ወደ ሐረር ለሚደረገው ሀገር አቀፍ ውድድር ሽኝት ተደረገለት

መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በሐረሪ ክልላዊ መንግስት አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 23ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል የሚሳተፈው የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ስፖርት ልዑካን ቡድን የሽኝት መርሃ ግብር ተከናወነ።

በአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በተካሄደው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የቢሮ አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ባህል ስፖርት ፌዴሬሽን አመራሮች፣ አሰልጣኞች እና ስፖርተኞች ተገኝተዋል።

በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ለልዑካን ቡድኑ አባላት የማበረታቻ መልዕክትና የቀጣይ ስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

አቶ ዳዊት በመልዕክታቸው ስፖርተኞቹ በውድድር ቆይታቸው ስፖርታዊ ጨዋነትን ቀዳሚ በማድረግ የከተማ አስተዳደሩን ስም እንዲያስጠሩና ውጤት ይዘው እንዲመለሱ አሳስበዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም የባህል ስፖርት ቡድኑ የአዲስ አበባ አምባሳደር በመሆን ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

አዲስ አበባ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መገለጫ እንዲሁም የሁለንተናዊ እድገት ማዕከል መሆኗን በሚያስተዋውቁ ተግባራት ላይ በንቃት እንዲሳተፉም አቅጣጫ አመላክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ ሀገር አቀፍ ውድድር ላይ በ12 የስፖርት አይነቶች የሚወዳደሩ ሲሆን ከ100 በላይ ልዑካንን ቡድን አባላትን ያሳትፋል።

ልዑካን ቡድኑ የፊታችን ቅዳሜ ወደ ሐረር ከተማ የሚያመራ ሲሆን፣ በቆይታውም ከሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከሚመጡ ስፖርተኞች ጋር ወንድማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ ለድል እንደሚወዳደሩ ይጠበቃል።

ለበለጠ መረጃ

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.