ማዕከሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ360ሺ በላይ ተጠ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ማዕከሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ360ሺ በላይ ተጠቃሚዎች አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

ማዕከሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ360ሺ በላይ ተጠቃሚዎች አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ባለፉት ዘጠኝ ወራት በስልጠና፣ በውድድር፣ በካፌ እና ሬስቶራንት ከ360ሺ በላይ ደንበኞች አገልግሎት ማግኘታቸውን አስታወቀ

ማዕከሉ የተሰጠውን ዋና ተልዕኮ ለማሳካት በመደበኛ እና በልዩ ስልጠና በ12 የስፖርት አይነት ታዳጊዎችን በብዛት እና በጥራት ለማፍራት እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት የአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይሉ ግርማ በአካል ብቃት እንቅቃሴ፣ በስልጠና፣ በውድድር፣ በጌም ዞን፣በመኝታ፣እና በሬስቶራንት ከ360ሺ በላይ ደንበኞች አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በቀደምትነቱ ተጠቃሽ የሆነውን ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ዘመኑ በሚፈቅደው ሁኔታ ለማስኬድ እና ምድረ ጊቢውን ለማስዋብ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹት አቶ ኃይሉ አቅም በፈቀደ መጠን ሳቢ እና ማራኪ ለማድረግ እንዲሁም የቢሮው ኢንሼቲቭ የሆነው የከርሰ ምድር ውሃ ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ አሳውቀዋል፡፡

ማዕከሉ ባለው ውስን ቦታ ከተማ ግብርናን ያስጀመረው የከተማ ግብርና የማስፋፋት ስራ እንደሚሰራ ያመላከቱት አቶ ኃይሉ ተቋሙ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ እና ቢሮ የሚያስተላልፋቸውን መመሪያዎች በመተግበር የተሰሩ ስራዎች ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ ዕድገት አኳያ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ጊቢውን ለማደስ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑን ላይ አጽንኦት የሰጡት ሥራ አስኪያጁ በስፖርት መሰረተ ልማት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ፣ ወጣቶችን ለማነጽ፣ እና ታላላቅ ፌስቲቫሎችን የማካሄድ ስራ በስፋት እንደሚሰራ ይፋ አድርገዋል፡፡

ማዕከሉ ስፖርትን በሰለጠነ መንገድ ለመምራት፣ ታዳጊዎችን ለማብቃት፣የስፖርት ባለሙያዎች አቅም ለማጎልበት እና ከወላጆች ጋር በመቀናጀት ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ያስታወሱት አቶ በኃይሉ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ አሻራ የማሳረፍ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮ ተጠቃሚ አሜን ያጆ በበኩሏ ለስፖርተኛ ምቹ የሆነው ቦታ በመስተንግዶ በምግብ እና በመኝታ በሚሰጠው አገልግሎት ደስተኛ መሆኗን ገልጻለች።

ወጣቶች፣የስፖርት ቤተሰቦች አንጋፋ ሰዎች ማዕከሉ በሚሰጠው የካፌ አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ እየተጠቀሙ እንደሚገኝ ያረጋገጡልን የማዕከሉ የረዥም ጊዜ ደንበኛ የሆኑት አቶ ደበበ እንግዳወርቅ የደሃ መግልገያ የሆነው መዕከል ይበልጥ እንዲስፋፋ አስፈላጊው እግዛ እና ድጋፍ ሊደረግበት እንደሚገባ ነግረውናል

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.