የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ጋር ያደረገው ስምምነት ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ጋር ያደረገው ስምምነት ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ
መጋቢት 21 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የመዲናዋን ስፖርታዊ እድገት ለማፋጠንና የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጋር የጀመረው የጋራ ስራ ውጤታማ መሆኑን አስታወቀ።
ይህ ቅንጅት በተለይም በከተማዋ ትኩረት የተሰጣቸውን የኮሪደር ልማት ውጤቶች ህያው በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ባለፉት ቀናት በተከናወኑ ተግባራት፣ በተፅዕኖ ፈጣሪዎቹ አማካኝነት በኮሪደር ልማቱ የተገነቡ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የወንዝ ዳርቻዎች እና ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያዎች የወጣቶች የክህሎት መግለጫና የልምድ ልውውጥ መድረኮች እንዲሆኑ ተደርጓል።
በተለይም ልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎችና የፌስቲቫል ዝግጅቶች በእነዚህ ስፍራዎች እንዲካሄዱ በማድረግ፣ አካባቢዎቹ ለወጣቶች ምቹና ማራኪ የፈጠራ ማዕከላት መሆናቸው ግንዛቤ ተፈጥሯል።
በተጨማሪም አስተዳደሩ በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የገነባቸው የስፖርት ማዘውተሪያዎች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ በማስተዋወቅ ረገድ የተፅዕኖ ፈጣሪዎቹ ድርሻ የላቀ ነበር።
በዚህም ወጣቶች ወደ ስፖርት ማዘውተሪያዎችና የክህሎት ማሳደጊያ ማዕከላት በብዛት እንዲመጡ ማድረግ ተችሏል።
ቢሮው ይህንን ውጤታማ አጋርነት አጠናክሮ በመቀጠል፣ ለተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የመዲናዋን ወጣቶች ተስፋና ተነሳሽነት ይበልጥ ከፍ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጧል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.