የአዲስ አበባ የስፖርት መሰረተ ልማቶች፤ ለጤናማ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአዲስ አበባ የስፖርት መሰረተ ልማቶች፤ ለጤናማ ማህበረሰብ እና ለስፖርት ቱሪዝም ያላቸው ፋይዳ

የአዲስ አበባ የስፖርት መሰረተ ልማቶች፤ ለጤናማ ማህበረሰብ እና ለስፖርት ቱሪዝም ያላቸው ፋይዳ

መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በመዲናዋ እየተገነቡ የሚገኙ ዘመናዊ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት ባለፈ፣ ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር እንዲሁም አዲስ አበባን የዓለም አቀፍ ስፖርት ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው።

ከተማዋ በቅርቡ የአፍሪካ ታዳጊ ወጣቶች የኦሎምፒክ ጨዋታን እና የአህጉራዊ የባህል ስፖርት ውድድሮችን እንድታዘጋጅ መመረጧ፣ በመሰረተ ልማት ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የሚያሳይ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።

ይህም አዲስ አበባን በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የስፖርት ውድድር መዳረሻ እያደረጋት ይገኛል።

በመዲናዋ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የስፖርት ማዘውተሪያዎች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ፣ በሰው ሰራሽ ሳርና በዘመናዊ የመሮጫ መስመሮች እየተገነቡ ይገኛሉ።

እነዚህ ማዕከላት ታዳጊዎችና ወጣቶች በአቅራቢያቸው ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ከማድረጋቸውም በላይ፣ ለብዙሃን አካል ብቃት እንቅስቃሴ (Mass Sport) መስፋፋት መሠረት ሆነዋል።

ይህም የዜጎችን ጤና ለመጠበቅና ንቁ አምራች ኃይል ለመፍጠር እየተከናወነ ባለው አገራዊ ተልዕኮ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አለው።

ከዚህ በተጨማሪ፣ በከተማዋ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የኮሪደር ልማት ለስፖርቱ ዘርፍ አዲስ ዕድል ይዞ መጥቷል። በልማቱ የተገነቡት ሰፊ የእግረኛ መንገዶችና የብስክሌት መሄጃዎች ስፖርት የነዋሪው የዕለት ተዕለት ባህል እንዲሆን ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል።

ይህ የተቀናጀ ልማት ከተማዋን ለስፖርት ቱሪዝም ምቹ ከማድረጉም በላይ፣ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በማስተናገድ ረገድ ያላትን ተወዳዳሪነት ይበልጥ ያጠናክረዋል።

በአጠቃላይ በመዲናዋ የተገነቡ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ለህብረተስቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ክፍት የተደረጉ ሲሆን፤ ለነገው ተተኪ ስፖርተኞች ጠንካራ መሰረት እየጣሉ ይገኛሉ።

እነዚህ ስራዎች አዲስ አበባን በዓለም መድረክ በስፖርት ቱሪዝም ዘርፍ በጉልህ እንድትታወቅና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቷን እንድታረጋግጥ የሚያየደርጋት ይሆናል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.